ሐይማኖት እና ሳይንስ (Religon vs Science) |HabeshasNetwork

Photo Courtesy of Jon Oleksiuk on YouTube

ይድረስ ለኢ-አማንያን፣

እንደሚገባኝ ከሆነ ለኢ-አማንያን ወይም athiest ለሆኑ ስዎች፣ እኛ በፈጣሪ የምናምን ሰዎች  እናሳዝናቸዋለን። የሚያዝኑልንም በምርምራቸው ፈጣሪያችንን ሊደርሱበት ስላልቻሉ፣ በቃ እኛንም የሌለውን ፈጣሪ አምላክ አለ ብለው በከንቱ ያመልካሉ፣ በከንቱ ይለፋሉ፣ በከንቱ ይጾማሉ፣ በከንቱ በሃይጢያት ይፀፀታሉ፣ በከንቱ ገንዘባቸውን በሃይማኖታዊ ነገርሮች ላይ ይጨርሳሉ እና ወዘተ ብለው በማሰብ፣ አትልፉ ከሞትን በኋላ ሌላ ህይወት የለም፣ ስለዚህ በሕይወት እስካለን ድረስ ማንንም ማምለክ ሳይኖርብን፣ ስለሐጢያት ምናምን ሳንጨናነቅ እድሜያችንን እንጨርስ ነው መልዕክታቸው በአጭሩ።

መልእክታቸውን በትህትና በመረዳት፣ እኔም እንደ ተዋህዶ ክርስቲያን athiest ለሆኑ ሰዎች አዝናላቸዋለሁ። ስለማዝንላቸውም ይህን መልእክት ለእነሱ ማስተላለፍ ግድ ይለኛል።  

በመጀመሪያ የሳይንስ ጥናት ስለብዙ ነገሮች በመፅሐፍ ቅዱስ በአጭሩ የተገለፁትን የሳይንስ ጥናት ደግሞ በስፋትና የእያንዳንዱን ነገር አሰራር ማሳየት መቻሉን አደንቃለሁ። ማለት መፅሐፍ ቅዱስ በሚገባን መልኩ ሁሉን በአጭሩ ይገልጻል እንጂ አንድ መጽሃፍ በመሆኑ መጠን ሁሉንም ነገር በስፋት አያሳየንም። በእርግጥ የተደጋገሙ የሚመስሉ 4ቱ ወንጌላት አሉ፣ ግን ያ የሆነበት የራሱ ምክንያትና ምስጢር አለው። እናም ለምሳሌ ያህል፣ መፅሃፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል ስለ እየሱስ ክርስቶስና ስለአደረጋቸው ተዓምራት ይናገርና በምእራፍ 21፡22 ላይ እንዲህ ይላል፣ “ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።”  ስለዚህ በአንዱ መጽሃፍ ቅዱስ እንኳን ስለሁሉም በስፋት መጻፍ ይቅርና እየሱስ ክርስቶስ ያደረጋቸው ተአምራቶቹ ብቻ ራሱ ተጽፎ እንደማያልቅ እንረዳለን።

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያዊው ተመራማሪ ዶ/ር ፋንታሁን አበበ ሲናገር፣ የሳይንስ ጥናት እራሱ ጅማሬው መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ወይም የመፅሐፍ ቅዱስን ሀሳብ የያዘ እንደሆነ ገልጾታል። ለምሳሌ የዝናብ አዘናነብ ከትን ወይም ከጉም እንደሚነሳ በሳይንስ እንረዳለን። በመፅሐፍ ቅዱስም ግን በአጭሩ እንዲህ ተገልጿል፣ “ጉም ከምድር ትወጣ ነበር፥ የምድርንም ፊት ሁሉ ታጠጣ ነበር” (ዘፍጥረት  2፡6)።

እና የሳይንስ ጥናት ስለተፈጥሮና የእያንዳንዱን ነገሮች አሰራር በስፋት ማስረዳቱ የሚደነቅ ነው ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር ፍጥረታትን እንደዚህና በዚህ መልኩ ነው የፈጠራቸው ማለት ሲገባቸው፣  atheist ሳይንቲስቶች ግን ከነአካቴው እግዚአብሔርን ከዚህ ሁሉ አውጥተው ነገሮች በራሳቸው እንደተፈጠሩ ያስተምራሉ። የሚገርመው ነገር የሳይንስ ጥናት ፍጥረታት እንዴት እንደተፈጠሩና እንደተባዙ ለመግለፅ ይሞክራል እንጂ ፍጥረታት ለምን ተፈጠሩ ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የለውም። የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ የሳይንስ ጥናት ስለስነፍጥረት የራሱ የሆነ አስተምህሮ ቢኖረውምና አስተምህሮውም ብዙ ዘመናትን ቢያስቆጥርም እስካሁን ድረስ ግን የፍጥረታት ጠንሳሹ ማን እንደሆነ ወይም አለም ሳይፈጠር በፊት እንዴትና የምን ሃይል የመጀመሪያውን ፍጥረት እንዲከሰት ያደረገው ምን ወይም ማን እንደሆነ እስካሁን ድረስ አልደረሱበትም። እንደርስበታለን ብለው እድሜ ዘመናቸውን አባክነው እየሞቱ ብዙ ዘመናት ተቆጥረዋል። አሁንም ሳይደርሱበት እድሜያቸውን እየጨረሱ ነው ያሉት። ፈጣሪያቸውን ክደው እየሞቱ ነፍሳቸው ምን ያህል አደጋ ላይ እየጣሉ እንደሆነ አያስቡም፣ ማሰብም አይፈልጉም።  የሚያሳዝነው ነገር ያ ነው።

እኔ ለatheist ሰዎች ጥያቄ አለኝ፡

ከሞት በኋላ ሌላ ሕይወት ወይም afterlife ይኑር አይኑር ሁለታችንም (ማለትም አማኞችና ኢ-አማንያን) ማስረጃ የልንም እንበልና፣

እስቲ እኛ አማኞች ፈጣሪ አለ ብለን በአምልኮት ዘመናችን ብንጨርስ የሚጎድልብንን ወይም በማመናችን ሊገጥመን የሚችለውን አደጋ እና እናንተ ደግሞ ባለማመናችሁ የሚገጥማችሁን አደጋ እናነፃፅር።

እኛ አማኞች ሳይንሳዊ ማስረጃ ባይኖረንም የምናምነው እንዲህ ነው፡

እንዴት እንደፈጠራቸው ለጊዜው እንዝለለውና፣ እግዚአብሔር አምላክ አዳምና ሔዋንን ፈጠረ፣ እነሱም በገነት ይኖሩ ነበር። ሞትም አልነበረም። አዳምና ሔዋን ጥፋት አጥፍተው በአጠፈቱም ጥፋት ከገነትም ተባርረው ሞትን አመጡ። ለትውልድም ሁሉ ሐጥያትን አወረሱ። ስለዚህ እግዚአብሔር ወልድ ከእርሷ ተውልዶ ሊያድነን ከመረጣትና ከውርስ ሐጥያት ከተጠበቀችው በቀር ሁላችንም የውርስ ሐጢያት አለብን። ገነትም ዝግ ሆነች። አምላካችን ግን በዚሁ ሁኔታ ጨክኖ አላስቀረንም። ከ5500 አመተ ፍዳ በኋላ በግዳጅ ሳይሆን ከፍቅሩ የተነሳ፣ እኛን ለማዳን ከአዘጋጃት ንጽህት ሁሉን ቻይ በመሆኑ ያለወንድ ዘር ተወልዶና እንደኛ ሰው ሆኖ፣ ሳይበድል በደላችንን ተሽክሞ፣ በመስቀል ላይ ሞቶ ዋጋ ከፍሎልን ዳግም ወደ ገነት የምንመለስበትን እድል ሰጠን፣ ዋጋውን ከፈለልን። ያንን ዋጋና እድል ተጠቅሞ ወደገነት ለመመለስ ግን የግድ ዋጋው ለእኛ እንደተከፈለ አምነንና እድሉን ለማግኘት ጥረት ያስፈልጋል። በአግባቡ ጥረን እድሉን የምናገኝበትንም መንግድ ወይም መረጃ ደግሞ አምላካችን አዘጋጅቶልናል። ያም መፅሐፍ ቅዱስ ነው። ይህን ሁሉ ዋጋ ከፍሎልንም ግን እንድንጠቀምበት አላስገደደንም። የመጠቀምም ያለመጠቀምም ምርጫ ሰጠን እንጂ። እድሉን አምነው የተጠቀሙት በገነት ዘልአለማዊ ሕይወትን ያገኛሉ። ያልተጠቀሙት ደግሞ ከምድራዊው ሞት በኋላ እንደእንክርዳድ ተለቅመው ወደ ገሃነም ዘልአለማዊ እሳት ይጣላሉ ብለን እናምናለን።

እናም ወደጥያቅዬ ስመለስ፣ እኛ አማኞች እንደምናምነው ከሞት በኋላ ሌላ ህይወት ከአለ፣ በምድር ላይ እያለን አማላካችን የሰጠንን እድል በአግባቡ እስከተጠቀምን ድረስ ከሞት በኋላ የሚጠብቀን በገነት ዘልአለማዊ ሰላም የሚገኝበት ሕይወት ነው። እናንተ እንደምትገምቱት ከምድራዊው ሞት በኋላ ሌላ ሕይወት ባይኖርም ደግሞ የሚጠብቀን አደጋ አይኖርም። ለእናንተ ግን እንደምትገምቱት ከምድራዊ ሞት በኋላ ሌላ ሕይወት ከሌለ እስየው፣ ምንም ሚያሳስብ ነገር አይኖርም። ግምታችሁ ልክ ካልሆነ ግን ትልቅ አደጋ ይጠብቃችኋል፣ ለዛውም ነፍሳችሁ ሳትሞት ለዘልአለም የምትቃጠሉበት የገሃነም እሳተ ጎመራ። ስለዚህ እነዚህ ሁለቱን ግምቶች ብናነፃፅር የቱ ያዋጣል? እስከመቼ ድረስ የፍጥረት ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር መሆኑን ክዳችሁ ግን እስካሁን ድረስ ተመርምሮ ያልተደረሰበትን ነገር በመመራመር እንደካዳችሁ እድሜአችሁን ትጨርሳላችሁ? የዚህ አለም ኑሮ አንዴ ብቻ ነው። እናም እኔ እንደ አንድ አማኝ ነፍሳችሁ ምን ያህል አደጋ ላይ እየወደቀ እንደሆነ ታስቡበት ዘንድ ምክሬ ነው!

የሁሉ ፈጣሪ አምላክ ትክክለኛውን መንገድ ይምራን፣ አሜን!

-ዩሔ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s